የድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ በከባድ ዝናብ ምክንያት አይካሄድም- አክሲዮን ማህበሩ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2017 (ኢዜአ):-  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ መካከል ሊደረግ የነበረው ጨዋታ በሃዋሳ ከተማ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት እንደማይካሄድ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።  

የጨዋታው ዳኞች በዝናቡ ምክንያት የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደማያጫውት በመወሰናቸው ጨዋታው እንደማይደረግ ገልጿል። 

በቀጣይ የጨዋታ ቀን እና ሰዓት ውሳኔ ይፋ እንደሚደረግ ማህበሩ በመረጃው አመልክቷል።

በተያያዘም ዛሬ በተደረገ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን አዳማ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም