ቀጥታ፡

እድሳት የተደረገለት የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2017 (ኢዜአ)፦ እድሳት የተደረገለት የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ሐውልት ዛሬ ተመርቋል።

እድሳቱ ሙዚየም እና አዳራሽን ያካተተ መሆኑም ተገልጿል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ አምባሳደሮች፣ የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማች ልጆችና የልጅ ልጆች ተገኝተዋል።


 

የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች አኩሪ ገድል ክብሩ ተጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ  ሐውልቱ ታሪኩን በሚመጥን መልኩ እድሳት እንደተደረገለት የወርልድ ቱጌዘር ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ማስተር ሊ ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ እድሳቱ የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክር ጠቅሰው ለፕሮጀክቱ ትግበራ ስኬት የኮሪያ አርበኞችና ዘማቾች ማህበርን አመስግነዋል።

የኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝዳንት ኮሎኔል እስጢፋኖስ ገብረመስቀል ሐውልቱ ትውልዱ ታሪኩን አውቆ ሀገር የማነፅ ተግባር እንዲወርስና የጀግኖችን አኩሪ ታሪክ ማስቀጠል እንዲችል የሚያነሳሳ እንደሆነ መግለጻቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም