በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በቱሪዝም ዘርፉ ስኬታማ አፈጻጸም ተመዝግቧል - ኢዜአ አማርኛ
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በቱሪዝም ዘርፉ ስኬታማ አፈጻጸም ተመዝግቧል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2017(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በቱሪዝም ዘርፉ ስኬታማ አፈጻጸም መመዝገቡን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ሀገራዊ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄዷል።
በግምገማው ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንዲሁም የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይም የቱሪዝም ሚኒስቴር የግብይት እና ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸምን ከዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ሁኔታ አንጻር የቱሪዝም ዘርፉ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች ያነሱ ሲሆን በሁሉም ደረጃ ውጤታማ አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት እንደ ሀገር ዘርፈ ብዙ ስኬቶች መመዝገባቸው በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
ከዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያ የኢትዮጵያ እድገት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ ውጤቶች እንደተገኙ የቱሪዝም ሚኒስቴር በመረጃው አመልክቷል።