ኢትዮጵያ መድን የሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ መድን የሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን አዳማ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ አበራ፣ ሀይደር ሸረፋ እና ያሬድ ካሳዬ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ስንታየሁ መንግስቱ ለአዳማ ከተማ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን በ48 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። በሊጉ 14ኛ ድሉን አሳክቷል።
በአንጻሩ በሊጉ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በ25ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።