ቀጥታ፡

ብሔራዊ ባንክ የ70 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ነገ ያካሂዳል

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 8/2017(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ70 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ነገ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ጨረታው ባንኩ በየሁለት ሳምንት መደበኛ እና ተከታታይ የሚያካሂደው የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ አካል መሆኑን ገልጿል።

በነገው ጨረታ 70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለጨረታ እንደሚቀርብ እና ፍላጎት ያላቸው ባንኮች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

ባንኩ በየሁለት ሳምንት መደበኛ እና ተከታታይ የሚያካሂደው የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ በማዕከላዊ ባንክ እየተከማቸ ካለው የውጭ ምንዛሪ የተወሰነውን መጠን ለግሉ ዘርፍ ለማቅረብና የባንኩን የገንዘብ ፖሊሲ ዓላማ ለማሳካት እንደሚረዳ ተመላክቷል።

ጨረታው የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና ሪፎርሙ ከተጀመረ ወዲህ መሻሻል እያሳየ የመጣውን የውጭ ክፍያ ሚዛን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳ ታምኖበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም