ቀጥታ፡

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ልዑክ የኤጀንሲውን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኘ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2017(ኢዜአ):- በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሲቪል ምዝገባ ተቋም(Office of Identification of the Population) ዋና ዳይሬክተር ሪቻርድ ኢሉንጋ የተመራ ልዑክ በአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ጉብኝት አድርጓል።

የልዑኩ የኢትዮጵያ ጉብኝት የኢትዮጵያን የዲጂታል ስርዓት ግንባታ ልምድ መቅሰምን አላማ ያደረገ መሆኑን የኤጀንሲው መረጃ ያመለክታል።

ልዑኩ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከሲቪል ምዝገባ ተቋም፣ ከሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ከቴሌኮም እና ፖስታ አገልግሎት እንዲሁም ከቴክኖሎጂ ትግበራ ተቋማት የተውጣጣ መሆኑ ተጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ከልዑኩ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ ዮናስ በሲቪል ምዝገባ ስርዓት እና በፋይዳ የጋራ ቅንጅት፣ የኩነት ምዝገባ ሽፋን እና አመዘጋገብ፣ የጤና ተቋማት ቅንጅት እንዲሁም ለተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የሚደረገውን ድጋፍ በተመለከተ የመዲናዋን ልምድ ማካፈላቸውን የኤጀንሲው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም