መቻል ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሽመልስ በቀለ በ72ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ መቻል በሊጉ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል። በ35 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል።


 

ቡድኑ በውድድር ዓመቱ 9ኛ ድሉንም አሳክቷል።

በአንጻሩ በሊጉ 9ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ34 ነጥብ ከ6ኛ ደረጃ ወደ 7ኛ ዝቅ ብሏል።

ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም