ኢትዮጵያ ቡና ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ ያደረገበት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል 

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 7/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ጋናዊው አጥቂ ኮንኮኒ ሀፊዝ በ24ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ39 ነጥብ ደረጃውን ከ4ኛ ወደ 2ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም 11ኛ ድሉን አሳክቷል። 

በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ 8ኛ ደረጃን ይዟል።

ምሽት 12 ላይ መቻል ከአርባምንጭ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም