የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ተጠባቂ የመልስ ጨዋታዎች - ኢዜአ አማርኛ
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ተጠባቂ የመልስ ጨዋታዎች

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2017 (ኢዜአ):- በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ።
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሲግናል ኡዱና ፓርክ ስታዲየም ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከባርሴሎና የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ባርሴሎና በሜዳው 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
43 ዓመቱ ጣልያናዊ ማውሪዚዮ ማሪያኒ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።
በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት በቪላ ፓርክ ስታዲየም አስቶንቪላ ከፒኤስጂ ይጫወታሉ።
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ባካሄዱት ጨዋታ ፒኤስጂ 3 ለ 1 ማሸነፉ አይዘነጋም።
የ41 ዓመቱ ስፔናዊ ሆዜ ማሪያ ሳንቼዝ ሂሜኔዝ የጨዋታው የመሐል ሜዳ አለቃ ናቸው።
ባርሴሎና እና ፒኤስጂ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ሰፊ እድል ይዘው ወደ ሜዳ ይገባሉ።
ነገ ሪያል ማድሪድ ከአርሰናል እና ኢንተር ሚላን ከባየር ሙኒክ የሚያደርጓቸው የመልስ ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው።