ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዚያ 19 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 7/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዚያ 19/ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በተመለከተ መግለጫ ተሰጥቷል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አበባ ታመነ እንደገለጹት፥ የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዚያ 19 ቀን 2017 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይካሄዳል።

ውድድሩ ገቢ ምርትን በመተካት የተሰማሩ የአገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች የስፖርት አልባሳትን ማስተዋወቅ እና የማምረት አቅማቸውን ማሳየትን አላማ አድርጎ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ችግሮች ለመፍታት እና ዘርፉን ለማሳደግ የተጀመረው የኢትዮጵያን ታምርት ንቅናቄ ማስተዋወቅ ሌላው የውድድሩ አላማ መሆኑን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሩ ከ13 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉበትም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም