ቀጥታ፡

በኮምቦልቻ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስተካከል ተችሏል

ደሴ፤ሚያዚያ 7/2017(ኢዜአ)፡- በኮምቦልቻ የሃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስተካከል መቻሉንን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የሰሜን ምስራቅ ሪጅን አንድ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በኮምቦልቻ አንድ እና ኮምቦልቻ ሁለት 132 ኬሎ ቮልት ሀይል ተሸካሚ መስመር ላይ ብልሽት አጋጥሞ ነበር፡፡

በተደረገ ጥረት ስርቆት የተፈጸመባቸውን ሁለት የሀይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች/ታወሮች/ አንዱን በመጠገን፣ ሁለተኛውን ደግሞ በእንጨት ፖል በመተካት በጊዜያዊነት ሃይሉን በማስተካከል አገልግሎቱን ማስጀመር መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች፣ በደቡብ ወሎ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎችና ከተሞች የተቋረጠባቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ፤ ህብረተሰቡ በትዕግስት በመጠበቁ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ የእንጨት ምሰሶውን   ወደ ብረት ታወር ለመቀየር እንደሚሰራ ጠቁመው፤  በመሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት ሲፈፀም  ለህግ አካል መጠቆም ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኮምቦልቻ  የሃይል ተሸካሚ መስመር ላይ   ባጋጠማ  ብልሽት የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማስተካከል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን  ትናንት  መዘገባችን ይታወሳል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም