ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው  በቬይትናም ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው 

 አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2017 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው  በቬይትናም ሀኖይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ2025 የፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ ላይም እንደሚሳተፉም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በቆይታቸው ከቬይትናም የፀሃይ ኃይል ማመንጫዎች በማምረት ወደ ውጭ የሚልከውን ቶዮ ሶላር የተባለውን ፋብሪካ ጎብኝተዋል።


 

ድርጅቱ በቅርቡ በሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በመግባት በኢትዮጵያ ሥራ መጀመሩን የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅቱ ከፀሃይ ኃይል ማመንጫ ምርት ባሻገር የኃይል ማመንጫ ፋብሪካ እንዲያቋቁም ጥሪ አቅርበዋል።

ይኽም ኢትዮጵያ ከያዘችው የአረንጓዴ አሻራ ፖሊሲ ጋር የተናበበ በማደግ ላይ ላለው የኃይል ጥያቄም ምላሽ በመስጠት ሊያግዝ እንደሚችልም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም