የፕሪሚየር ሊጉ የሶስተኛ ቀን መርሃ ግብር እነማንን ያገናኛል? - ኢዜአ አማርኛ
የፕሪሚየር ሊጉ የሶስተኛ ቀን መርሃ ግብር እነማንን ያገናኛል?

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
የዕለቱ የመጀመሪያ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ያገናኛል።
ኢትዮጵያ ቡና በ36 ነጥብ 4ኛ ደረጃን ሲይዝ ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ኢትዮጵያ ቡና ካሸነፈ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ ያደርጋል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቻል ከአርባምንጭ ከተማ ይጫወታሉ።
መቻል በ32 ነጥብ 9ኛ፣ አርባምንጭ ከተማ በ34 ነጥብ 6ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በተያያዘም ትናንት በተደረጉ የ25ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን፣ ሲዳማ ቡና ባህር ዳር ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።