ናፖሊ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2017 (ኢዜአ)፦ በጣልያን ሴሪአ የ32ኛ ሳምንት መርሃ ግብር  ናፖሊ ኢምፖሊን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስኮት ማክቶሚናይ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሮሜሎ ሉካኩ ቀሪዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ናፖሊ ነጥቡን ወደ 68 ከፍ አድርጓል። ከሊጉ መሪ ኢንተር ሚላን ያለውን ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ ብሏል።

ኢምፖሊ በ24 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በሌላ በኩል በስፔን ላሊጋ የ31ኛ ሳምንት ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ ሪያል ቫላዶሊድን 4  ለ 2 አሸንፏል።

ሁሊያን አልቫሬዝ ሁለት ግቦችን በፍጹም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር ጁሊያኖ ሲሞኒ እና አሌክሳንደር ሰርሎዝ ቀሪዎቹን ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ማመዱ ሲያላ በፍጹም ቅጣት ምት እና ዣቪ ሳንቼዝ ለሪያል ቫላዶሊድ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

ውጤቱን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አትሌቲኮ ማድሪድ ነጥቡን ወደ 63 ከፍ አድርጓል።

ሪያል ቫላዶሊድ በ16 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ባርሴሎና በ70 ነጥብ አንደኛ እና ሪያል ማድሪድ በ66 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት ጨዋታ ደግሞ ቦርንማውዝ ፉልሃምን በአንቶዋን ሴሜንዮ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም