ሃዋሳ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዓሊ ሱሌይማን በ47ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።

ዓሊ በ37ኛው ደቂቃ ሃዋሳ ከተማ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት መጠቀም አልቻለም።

ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በሊጉ ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። ቡድኑ ድል ቢቀናውም በ24 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዞ አሁንም ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ወላይታ ድቻ በ37 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል።

ዛሬ በተደረጉ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲሁም ሲዳማ ቡና ባህር ዳር ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም