ሲዳማ ቡና ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል 

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት  ጨዋታ ሲዳማ ቡና ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን በ24ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ቡድኑን ባለድል አድርጓል። 

ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በሊጉ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል። ቡድኑ በ32 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 10ኛ አሻሽሏል።

ሽንፈት ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በ37 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዟል። 

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሃዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ጋር ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም