የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ተጠናክሮ ይቀጥላል- አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ተጠናክሮ ይቀጥላል- አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ወዳጅነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ገለጹ።
አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ካሚል ኦማር ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
አምባሳደር ብርሃኑ፥ በጂቡቲ የስራ ቆይታቸው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር ላበረከቱት ወንድማዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ዓመት ወዳጅነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውንም በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሃብት ማኔጅመንት እና አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው።