ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ኪርጊስታን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ምክክር አደረጉ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ኪርጊስታን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ምክክር አድርገዋል።

በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በጣሊያን የኪርጊስታን አምባሳደር ከሆኑት ታላይ ባዛርቤይቭ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም፥ የሁለቱን ሀገራት የጋራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ያላቸውን መደጋገፍ የበለጠ ለማጠናከር ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።

አምባሳደር ደሚቱ በወቅቱ ፥ ኪርጊስታን ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፈት ለያዘችው እቅድም ሂደቱን ለማፋጠን አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ማረጋገጣቸውን በሮም ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም