ቀጥታ፡

ለምርት ዘመኑ ወደ ሀገር ውስጥ ከ1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ማዳበሪያ ተጓጉዟል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በ2017/18 የምርት ዘመን  እስከ አሁን  ከ1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን አስታወቀ።

መንግስት ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን (24 ሚሊዮን ኩንታል)  የአፈር ማዳበሪያ ገዝቶ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እቅድ ይዟል።


 

ከተያዘው እቅድ ውስጥ እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከ1 ሚሊዮን 34 ሺህ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን ባለስልጣኑ ገልጿል።

39 ሺህ 764 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ላይ እንደሚገኝም አመልክቷል።

የዩሪያ እና ዳፕ ማዳበሪያው በድንበር የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ እና በባቡር  መጓጓዙን የባለስልጣኑ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም