የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አባልነት ጥያቄ ድጋፍ እንድምትሰጥ ገለጸች - ኢዜአ አማርኛ
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አባልነት ጥያቄ ድጋፍ እንድምትሰጥ ገለጸች
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አባልነት ጥያቄ በቦርዱ እንዲቀርብ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች።
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን(ዶ/ር) ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የፋይናንስ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ግንኙነት ዳይሬክተር እና የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ ተወካይ ቱራያ አልሃሺሚ ጋር ተወያያተዋል፡፡
አምባሳደር ዑመር ኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አባል ለመሆን እያደረገች ላለው ጥረት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድጋፍ እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ዳይሬክተሯ እና የባንኩ ተወካይ በበኩላቸው የኢትዮጵያን የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጥያቄው በቦርዱ እንዲቀርብ ሀገራቸው ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል፡፡
የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ በብሪክስ ማዕቀፍ የሕዝብና የግል ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ዓለም አቀፍ ልማትን እንዲያበረታታ ታስቦ እ.አ.አ በ2014 የተቋቋመ የባለብዙ ወገን ልማት ባ