ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዩጋንዳዊው አጥቂ ሳይመን ፒተር በ21ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ35 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል።
በሊጉ ዘጠነኛ ድሉንም አሳክቷል።
በአንጻሩ በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ31 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ይዟል።
የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከሰዓትም ሲቀጥል ሲዳማ ቡና ከባህር ዳር ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት፣ ሃዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ምሽት 12 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።