ቀጥታ፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት በአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ዘጠኝ ወራት እቅድ ክንውን ሪፖርት ላይ እየመከረ ነው።


 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) እንደገለጹት በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶች እና የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት ውይይት ይደረግባቸዋል።

በሰላም፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ግንባታ እና ዜጎችን ተጠቃሚ ባደረጉ የማህበራዊ ልማት ስራዎች ላይ ግምግማ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በክልሉ ለውሳኔ የቀረቡ የኢንቨስትመንት ፍላጎቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም