ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ብራዚል በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚል የመከላከያ ሚኒስትር ሆዜ ሙሲዮ ሞንቴሮ ፊልሆ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ልዑልሰገድ የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት በሰላም እና ደህንነት ዘርፍ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እና ብራዚል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች አባል ሀገራት መሆናቸውን አውስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም