የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ሽልማቶችን አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ሽልማቶችን አገኘ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አየር መንገድ እና በአፍሪካ በቀዳሚነት በተረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኖቹ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች ሁለት ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡
አየር መንገዱ በጀርመን ሀምቡርግ በተካሄዱ ሁለት መርሐግብሮች ላይ ነው በአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አየር መንገድ እና በአፍሪካ በቀዳሚነት በተረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኖቹ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች “Cabin Concept of the Year 2025” ሽልማቶችን የተቀበለው፡፡
እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያጎናፀፉና በዓለም ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡