የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡


 

አምባሳደር ብርሃኑ ጂቡቲ በነበራቸው ቆይታ ከጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተቀራርቦ በመስራት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ስለመቻሉም አመላክተዋል።

አምባሳደር ብርሃኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኃብት ማኔጅመንትና አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም