በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሆሳዕና በዓል እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሆሳዕና በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 5/2017(ኢዜአ)፦የሆሳዕና በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌል፣ የሀይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
ዕለቱ የዐቢይ ጾም የመጨረሻው ሳምንት እሁድ ላይ የሚውል ሲሆን ይህን ዕለት የኢትዮጵያ ካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል።
በዓሉ በፀሎት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና እና በሌሎች ሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።