የሊጉ የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 5/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጅማሮ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከስሑል ሽሬ ከቀኑ 9 ሰዓት፣ ሀድያ ሆሳዕና ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
መርሃ ግብሩ ነገም ቀጥሎ ሲውል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሲዳማ ቡና ከባህር ዳር ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የ25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ መድን በ45 ነጥብ ይመራል።
ባህር ዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻ በተመሳሳይ 37 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ሃዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ስሑል ሽሬ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ15ኛ እስከ 18ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።
የአርባምንጭ ከተማው አህመድ ሁሴን በ10 ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ይመራል።
የኢትዮጵያ ቡናው አንተነህ ተፈራ፣ የፋሲል ከነማው ጌታነህ ከበደ እና የሃዋሳ ከተማው ዓሊ ሱሌይማን በተመሳሳይ 9 ግቦችን በማስቆጠር ይከተላሉ።