ቀጥታ፡

የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጋራ ኮሚሽኑ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 4/2017 (ኢዜአ) ፦የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ በአምስተኛው የኢትዮ-አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሀደራ አበራ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የጋራ ኮሚሽኑ ስብሰባ ነገ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም