ማንችስተር ሲቲ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 4 /2017 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከመመራት ተነስቶ ክሪስታል ፓላስን 5 ለ 2 አሸንፏል።
በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢቤሬቺ ኢዜ እና ክሪስ ሪቻርድስ ባስቆጠራቸው ግቦች ክሪስታል ፓላስ 2 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር።
ይሁንና ኬቨን ደ ብሮይን፣ ኦማር ማርሙሽ፣ ማቴዎ ኮቫቺች፣ ጀምስ ማክቲ እና ኒኮ ኦራይሊ ከመረብ ላይ ያሳረፏቸው ጎሎች ሰማያዊዎቹ ውጤቱን ቀልብሰው አሸናፊ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ55 ነጥብ ደረጃውን ከ5ኛ ወደ 4ኛ ከፍ አሻሽሏል። በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርገው ጉዞ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
ክሪስታል ፓላስ በ43 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።