ኮሚሽኑ የአማራ ክልል አጀንዳዎችን ተረከበ - ኢዜአ አማርኛ
ኮሚሽኑ የአማራ ክልል አጀንዳዎችን ተረከበ
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 4/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአማራ ክልል አጀንዳዎችን ከምክክር ባለድርሻ አካላት ወኪሎች ዛሬ ተረክቧል።
የአማራ ክልል የምክክር መድረክ ከመጋቢት 27 እስከ ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም ድረስ በባህርዳር ከተማ ሲካሄድ ቆይቷል።
የአማራ ክክል የምክክር ባለድርሻ አካላት በመረጧቸው 25 ወኪሎች አማካኝነት የክልሉን አጀንዳዎች ለጠቅላላ ጉባኤው ካቀረቡ በኃላ በይፋ ለኮሚሽኑ አስረክበዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች መላኩ ወልደማርያምና ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) የክልሉን አጀንዳ ከተወካዮቹ መረከባቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።