ቀጥታ፡

የቶጎ ጫሌ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ዛሬ ይመረቃል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 4/2017 (ኢዜአ)፦የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታዎች  አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ፣   ሡልጣን ወሊ (ዶ/ር ኢ/ር) እና አቶ ሞቱማ መቃሳ የቶጎጫሌ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለማስመረቅ ጅግጅጋ ገብተዋል። 

አመራሮቹ ጅግጅጋ ጋራድ ዊልዋል ኤርፖርት ሲደርሱ የሶማሌ ክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮ አመራሮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም