ቀጥታ፡

አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር ይጫወታል 

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 4/2017 (ኢዜአ)፦የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በኤምሬትስ ስታዲየም አርሰናል ከብሬንትፎርድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በ62 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል ካሸነፈ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ስምንት ዝቅ ይደረጋል።

የ32ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ በኢትሃድ ስታዲየም ማንችስተር ሲቲ እና ክሪስታል ፓላስን ያገናኛል።

ጨዋታው ለሰማያዊዎቹ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ለሚያደርጉት ጉዞ ወሳኝ የሚባል ነው።

በሌሎች መርሃ ግብሮች ብራይተን ከሌይስተር ሲቲ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከኤቨርተን እና ሳውዝሃምፕተን ከአስቶንቪላ በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ነገ ከዌስትሃም ጋር ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም