የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያን የሁለትዮሽ የንግድ ትስስር ማጠናከርን ያለመ ውይይት ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያን የሁለትዮሽ የንግድ ትስስር ማጠናከርን ያለመ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 3/2017(ኢዜአ)፦ በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ገረመው በሌጎስ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጋብርኤል ኢዳሆሳ ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በአቡጃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ትስስር ማጠናከር ላይ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል።
የንግድ ምክር ቤቶች በሀገራዊ እና አህጉራዊ የንግድ ትስስር ላይ የሚሰሩባቸውን እድሎች ማመቻቸት በሚቻልባቸው አማራጮች ላይ መወያየታቸውን በአቡጃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
እ.አ.አ በ1888 የተቋቋመው የሌጎስ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የናይጄሪያን የግል ዘርፍ የሚወክል ግዙፍ ድርጅት ነው።
ምክር ቤቱ በንግድ፣ ኢንዲስትሪና ፋይናንስ አገልግሎት ላይ ያሉ ኩባንያዎችን የያዘ ሲሆን ከሁለት ሺህ በላይ አባላት አሉት።