ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራትን አጠናክሮ ይቀጥላል- ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 3/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የባህር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ ገለጹ።

የባህር ኃይል ስራን የተመለከተ ውይይት ተካሄዷል።

የባህር ኃይል ጽህፈት ቤት ሃላፊ ካፒቴን እንግዳው ወርቁ የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

ካፒቴን እንግዳው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የሰለጠነ የሰው ኃይል ልማት ሥራ፤ አቅም ግንባታ እና መሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ የሠራዊቱን ወታደራዊ ዝግጁነት በማሳደግ እና ራሱን በማጠናከር ረገድ ስኬታማ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ባህር ኃይ ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ባለፉት ጊዜያት በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል።

ባህር ኃይሉን ማጠናከርና ሰራዊቱ ተጨማሪ ጠንካራ ኃይል ለመሆን እያከናወነ ያለውን ዘርፈ ብዙ ስራ መደገፍ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና አዛዡ መግለጻቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም