አምባሳደር አደም መሀመድ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለቱርኪዬ ኩባንያዎች አስተዋወቁ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 2/2017(ኢዜአ)፦በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሀመድ በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ከተርኪዬ ኩባንያዎች ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ ከዘጠኝ ኩባንያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ በኤነርጂ፣ በኮንስትራክሽን፣ በጤና፣ ቱሪዝምና፣ አይሲቲ እንዲሁም ግብርና እና ማኑፋክቸሪንግ ዙሪያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን አስተዋውቀዋል።

ኩባንያዎች በቅርቡ በግንቦት ወር በኢትዮጵያ በሚካሄዱት የኢትዮጵያ ታምርት እና ኢንቨስት ኢትዮጵያ የቢዝነስ ፎረሞች ላይ እንዲሳተፉም አምባሳደሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የኤምባሴው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም