ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው 3 ሺህ 700 ኩንታል የኮንትሮባንድ ቡና ተያዘ - ኢዜአ አማርኛ
ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው 3 ሺህ 700 ኩንታል የኮንትሮባንድ ቡና ተያዘ
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው 3 ሺህ 700 ኩንታል የኮትሮባንድ ቡና በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።
የኮንትሮባንድ ቡናው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ-3 A.A 14081፣ ኮድ-3 A.A 43218 በሁለት ተሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ወደ ደብረብርሃን ከተማ ለመግባት ሲዘዋወር እንዲሁም ኮድ 3 A.A A34574 የሆነው ተሽከርካሪ ደግሞ የኮንትሮባንድ ቡናውን ጭኖ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር ሲጓዝ በሱልልታ የፍተሻ ጣቢያ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ሠራተኞች ጋር በመቀናጀት መያዛቸውን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ህብረተሰቡ ኮንትሮባንድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ተፅዕኖ በመገንዘብ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ስላለው ቀና ትብብር ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረበ ይህንኑም ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።