የናይጄሪያ ወታደራዊ ሪሶርስ ሴንተር የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የለውጥ ሥራዎችን ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
የናይጄሪያ ወታደራዊ ሪሶርስ ሴንተር የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የለውጥ ሥራዎችን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 1/2017 (ኢዜአ):-የናይጄሪያ ወታደራዊ ሪሶርስ ሴንተር ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የለውጥ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ዋና መምሪያ ተጠባባቂ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ደጀኔ በቀለ ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል አድርገዋል።
ረዳት ኮሚሽነሩ ስለ ተቋሙ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ዘመናዊ የፖሊስ መገናኛ ዲጂታል ሬድዮ፣ የኮማንድ ኮንትሮል ማዕከልን፣ የቀጥታ ጥቆማ መቀበያ 991፣ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) እና ዘመናዊ ካሜራና ሌሎች የደህንነት መሳሪያ የተገጠመላቸዉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላትም በጉብኝታቸው መደሰታችውን ገልጸው ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ምስጋና ማቅረባቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።