ጣና ነሽ ጀልባ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ ጀመረች - ኢዜአ አማርኛ
ጣና ነሽ ጀልባ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ ጀመረች

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦ ጣና ነሽ ጀልባ ከጂቡቲ ዶራሌ ፈርጀ-ብዙ ወደብ ወደ ሀገር ቤት ዛሬ ጠዋት ጉዞ ጀምራለች።
ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራትም ተገልጿል።
ጀልባዋ 150 ሜትሪክ ቶን ክብደት የምትመዝን፣ 38 ሜትር ርዝመት ያላት እና 200 ተሳፋሪ የመያዝ አቅም ያላት ናት።
ለጉዞ የሚሆን የዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ መስመሮች በኮሪደሩ የሚቋረጡና ተለዋጭ መንገድ የተዘጋጀላቸው ሲሆን፣ ሁለት ተጨማሪ ጎታች ተሽከርካሪዎች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ተመድቦ ከጀልባዋ ጋር ጉዞ መጀመሩ ተገልጿል።
ከጅቡቲ ተነስታ በዲኪል-ካላፊ መንገድ እንድምትንቀሳቀስ እና በአማካይ ከሰባት ቀናት በኃላ ኮሪደሩን ታቋርጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
የጣና ነሽ ጀልባ ላለፉት ጊዜያት አስፈላጊው ክትትል ሲደረግላት እንደቆየ እና በአማካይ ከሶስት ወራት በኃላ ጎርጎራ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።
ጀርባዋ ለመዝናኛ አገልግሎት በመጠቀም በኢትዮጵያ እያደገ ያለው የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ የማበርከት አቅም እንዳላት ኤምባሲው ገልጿል።