የአርሰናል እና ሪያል ማድሪድ ተጠባቂ ፍልሚያ - ኢዜአ አማርኛ
የአርሰናል እና ሪያል ማድሪድ ተጠባቂ ፍልሚያ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ።
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም አርሰናል ከወቅቱ የዋንጫው ባለቤት ሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ የዓለም የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ቀልብ ስቧል።
በጥሎ ማለፉ አርሰናል ፒኤስቪ አይድሆቨንን፣ ሪያል ማድሪድ የከተማ ተቀናቃኙን አትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ ማለፋቸው ይታወቃል።
የቦስኒያ እና ሄርዞጎቪኒያው ኢርፋን ፔልቶ ተጠባቂውን ጨዋታ በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።
በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት በአሊያንዝ አሬና ባየርን ሙኒክ ከኢንተርሚላን ይጫወታሉ።
መርሃ ግብሩ ነገም ቀጥሎ ሲውል ባርሴሎና ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ፒኤስጂ ከአስቶንቪላ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የመልስ ጨዋታዎች በቀጣዩ ሳምንት ይደረጋሉ።