ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃ ከተማ አዲስ በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃ ከተማ ከግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ የበረራ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል።

ይህ አዲስ የበረራ አገልግሎት በሳምንት ለአራት ቀናት የሚደረግ መሆኑንም አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጀምረው አዲስ የበረራ መስመር መንገደኞች በተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ የደማቅ ባህልና ሰፊ የኢኮኖሚ እድሎች ባለቤት ወደ ሆነችው ሻርጃ ከተማ በቀላሉ እንዲጓዙ እንደሚስችልም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም