ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመሰገኑ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በትግሪኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት 62 (9)፣ በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 15 (3) እና ደንብ ቁጥር  533/2015 እንዲሁም በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት መሠረት አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።


 

አቶ ጌታቸው በትግራይ ክልል የተገኘው ሰላም ወደ ኋላ አንዳይመለስ ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ለሰጡት አመራር የፌዴራል መንግስት እውቅና እንዳለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይም ተቀራርበው እንደሚሰሩ በማረጋገጥ ለነበራቸው ቆይታ አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም