በአማራ ክልል የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደቀጠለ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደቀጠለ ነው
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ የአማራ ክልል የምክክር መድረክ የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች ትናንት መጋቢት 28/2017 ዓ.ም በሶስት ክላስተር ተከፍለው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ውይይት ሲያጠናቅሩ መቆየታቸውንም አስታውሷል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ አነስተኛ ቡድኖች በተናጥል አጀንዳቸውን ለይተው ካጠናቀቁ በኋላ አንድ ንዑስ ቡድን በመመስረት አጀንዳዎቻቸውን በማጠናቀር ላይ ይገኛሉ ብሏል።
የአማራ ክልል የምክክር መድረክ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 27/2017 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በይፋ መጀመሩ ይታወሳል።