ቀጥታ፡

በክልሉ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ በሆሳዕና እየተካሄደ ነው

ሆሳዕና፤29/2017 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የምክክር መድረኩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በጋራ ያዘጋጁት ነው።

መድረኩ በክልሉ ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በተጨማሪ በአነስተኛ፤ በመካከለኛና በአምራች ኢንተርፕራይዞች የተሰማሩ ባለሀብቶችን ለማሳደግ ያለመ መድረክ መሆኑ ተጠቁሟል።

መድረኩ በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች መነቃቃትን ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና ልዩ ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም