የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፦ የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥቷል።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ቻም ኡቦንግ፦ የክልሉ አካባቢና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ
2.አቶ ኮንግ ጆክ፦ የክልሉ ከተሞች ፕላን ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር
3.አቶ ሙሴ ጋጄት ፦ የክልሉ መስኖና ቆላማ ቢሮ የመስኖ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ
4.ወይዘሮ ታቢታ ኡሪያሚ፦ ከተማ መሠ/ል/ቢሮ መሰረተ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ
5.ኢንጂነር ጓነር ጆክ፦ ከተማ መሠ/ል/ቢሮ የከተማ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ
6.አቶ ቦት ጋች፦ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ
7.ዶክተር ሞክ ያንግዶንግ፦ የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ
8.ወይዘሮ ኛልዊት ፓል፦ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር
9.አቶ ደሳለኝ ብሩ፦ የኢኖቬሽን ቴክ/ኮሚ/አይ ሲ ቲ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር
10.አቶ ኒያል ቶት፦ ኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዲን
11.አቶ ኮንግ ጋች፦ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር
12.አቶ ኡኬሎ ኡማን፦ የክልሉ የዲያስፖራ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ
13.አቶ ጋርዊች ጋች፦ የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
14.አቶ አቦር አሌክስ፦ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ተደርገው ተሾመዋል።
ሹመት የተሰጣቸው አመራሮች የትምህርት ዝግጅታቸው፣የአመለካከት ፣
የስራ ልምድና የመንግስት ተልዕኮን ማስፈጸም የሚችሉ እንደሆነ ተመላክቷል።