ቀጥታ፡

የ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት  የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 9 ሰዓት፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

መርሃ ግብሩ ነገም ቀጥሎ ሲውል አዳማ ከተማ ከወላይታ ድቻ ፣ ሀድያ ሆሳዕና ከድሬደዋ ከተማ እና መቻል ከመቀሌ 70 እንደርታ የሚጫወቱ ይሆናል።

የ24ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።

የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ መድን በ44 ነጥብ ይመራል።

ኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ በተመሳሳይ 36 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ሃዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ስሑል ሽሬ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ15ኛ እስከ 18ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።

የአርባምንጭ ከተማው አህመድ ሁሴን በ10 ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ይመራል።የኢትዮጵያ ቡናው አንተነህ ተፈራ በ9ኝ ጎሎች ይከተላል።

የመቀሌ 70 እንደርታው ያሬድ ብርሃኑ እና የሃዋሳ ከተማው ዓሊ ሱሌይማን በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር ቀጣዩን ደረጃ ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም