ሪያል ማድሪድ በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
ሪያል ማድሪድ በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2017 (ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ የ30ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሪያል ማድሪድ በሜዳው በቫሌንሺያ 2 ለ 1 ተሸንፏል።
ሁጎ ዱሮ እና ሙክታር ዲያካቢ የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ቪኒሸስ ጁኒየር ለሪያል ማድሪድ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል።
ቪኒሺየስ በጨዋታው ያገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ በ63 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል።
ቫሌንሺያ በ34 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።
የሊጉ መሪ ባርሴሎና ዛሬ ማምሻውን ሪያል ቤቲስን ካሸነፈ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ከፍ ያደርጋል።