ቀጥታ፡

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከሴናተር ቴድ ክሩዝ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2017(ኢዜአ)፦ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሴናተር ቴድ ክሩዝ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው በዋና ዋና የጋራ እና በተለያዩ ዘርፎች ትብብርን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

በአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴው ሥራ እንዲሁም ንዑስ ኮሚቴው አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ከማሳደግ አንጻር ያለውን ሚና አስመልክቶም ተወያይተዋል።

ሁለቱም ወገኖች በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የበለጠ ተቀራርበው ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

አምባሳደር ብናልፍ ከሴናተር ቴድ ግሩዝ ጋር ሲገናኙ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም