አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከቀድሞ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ጃክ ኪንግስተን ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከቀድሞ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ጃክ ኪንግስተን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2017 (ኢዜአ)፦ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከቀድሞ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ጃክ ኪንግስተን ጋር ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት በሚጠናከርበት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
በውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር፤ በአስተዳደሩ እና በምክር ቤቱ መካከል የተሻለ ትብብር ለመፍጠር በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ትኩረት በማድረግ መነጋገራቸው ተገልጿል።
አምባሳደር ብናልፍ የቀድሞው የምክር ቤት አባል ጃክ ኪንግስተን በኢትዮጵያ ዙሪያ ባላቸው ጥልቅ እውቀት እና እውነተኛ ስሜት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።