በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 27/2017(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።
በክልሉ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ የተሟላ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
የአጀንዳ ማሳባሰቡ በክልሉ 267 ወረዳዎች የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ከ4 ሺህ 500 በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ተሳታፊዎች መለየታቸውን ገልጿል።
ከመጋቢት 27 እስከ ሚያዚያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የማህበረሰብ ተወካዮችን ጨምሮ ተጽእኖ ፈጣሪ የማህበረስብ ክፍሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያካተተ 6 ሺህ ወኪሎች እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል።
ኮሚሽኑ ሕብረተሰቡ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በ10 ክልሎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች አጀንዳ ማሰባሰብ ስራ ማከናወኑ የሚታወስ ነው።