ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 122 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ለደንበኞቹ ድልድል አደረገ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 26/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 122 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ለደንበኞቹ ድልድል ማድረጉን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀገሪቱን የገቢ ንግድ ለማሳለጥ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ለደንበኞቹ እያቀረበ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ 711 የባንኩ ደንበኞች ያቀረቡትን ጥያቄዎች በመገምገም ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ 98 በመቶ የሚሆነውን መመለሱን አስታውቋል።

በዚህም ለደንበኞች በድምሩ የ122 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ድልድል ማድረጉን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የቀሩት ጥቂት ደምበኞች ጥያቄ ተጨማሪ የመረጃ ማጣራት ስራ ተሰርቶ በቅርቡ የሚታይላቸው ይሆናል ብሏል።

በቀጣይም ለደንበኞቹ የውጪ ምንዛሪ ጥያቄ፤ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ባንኩ ዝግጁ መሆኑንም ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም